ማክሰኞ ጥር 17 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ።
ትናንት ሌሊት ከወልድያ ወደ አዲስ አበባ 22 ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ አጣዬ ከተማ ሲደርስ በቦታው ቆሞ ከነበረ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የተከሰተው።
የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ሀላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ግዛቸው እንደገለጹት፥ በአደጋው የ5 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ 12 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳትና 5 ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።
በደረሰው አደጋ በውስጡ ያሉ 6 ህጻናት ምንም ጉዳት አልደርሰባቸውም።
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ሲሆን፥ ምናልባትም ከአቅም በላይ መጫንና ፍጥነት ሊሆን ኮማንደር ተስፋዬ ገልፀዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n



