ባለፉት 6 ወራት ከግብርናው ዘርፍ የውጭ ንግድ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለፀ

0
1234

ዕሮብ ጥር 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ባለፉት 6 ወራት ከግብርናው ዘርፍ ከውጭ ንግድ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የግብርና ሚኒስትር ዑመር ሁሴን ባለፉት ስድስት ወራት ከግብርናው ዘርፍ ከውጭ ንግድ ከፍተኛ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል።

ባለፉት 6 ወራት ከግብርና ዘርፉ ከውጭ ንግድ 1 ነጥብ 323 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፣ ይህም የዕቅዱ 109 በመቶ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የተገኘው ገቢ ከባለፈው አመት 6 ወር ጋር ሲነጻጸርም የ32 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱንም ገልፀዋል።

_____________________

ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here