ዕሮብ ጥር 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከዚህ ቀደም ባካሄድኩት ምርመራ ላይ ባልተካተቱ አካባቢዎች በጦርነቱ ምክንያት የተፈፀሙ ሰብኣዊ መብት ጥሰቶችን መርምሬ እያጠናቀቅኩኝ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ በጦርነቱ አካባቢ ስለተከሰተው የሰብኣዊ መብት ጥሰት ከተባበሩት መንግስታት ጽሕፈት ቤት ጋር በጣምራ ጥናት ማድረጉ ይታወሳል፡፡
በወቅቱ በነበረው ሁኔታ ምርመራው ተደራሽ ያልሆነባቸው በርካታ ሥፍራዎች እንደነበሩም ኮሚሽኑ አስታውቆ ነበር፡፡
ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ አብዛኞቹ የክልሎቹ አካባቢዎች በመንግስት ቁጥጥር ሥር በመሆናቸው ምርመራ እየተሰራ እንደሆነም ተነግሯል፡፡
በቅርቡ ሙሉ ጥናቱ ተጠናቆ ሪፖርቶቹ ይፋ እንደሚደረግም መገለጹን አሐዱ ዘግቧል፡፡
ኮሚሽኑ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ተደራሽ ቢሆንም አሁንም ለመስራት ያልቻለባቸው ሥፍራዎች እንዳሉም ጠቁሟል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n



