ዕሮብ ጥር 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የስዊዲን መንግስት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የስዊዲን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ ጋር በወደሙ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ዙሪያ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው ጥሪውን ያቀረቡት፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ የስዊዲን መንግስት ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ በርካታ ጥራት ያላቸው ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን አስታውሰው በአሁኑ ወቅት በህውሃት ቡድን የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ደረጃቸውን በጠበቀ ሁኔታ መልሶ ለመገንባት መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
የስዊዲን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ በበኩላቸው አገራቸው የትምህርት ተቋማትን በጥራት መልሶ ከመገንባት አንፃር ወደፊት ምላሽ እንደምትሰጥ ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ እስከአሁን ድረስ የሲዊዲን መንግስት ከ6 ሺህ በላይ ጥራታቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶችን መገንባቱን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




