ሰኞ ጥር 23 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ዳንኤል እንድሪስ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱም በክልሉ አሁን ላይ በተከሰተው ድርቅ ዙሪያ ሙስጠፌ ለልዑካን ቡድኑ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በዚህም በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች አፋጣኝ እርዳታ እንደሚያስፈልግ እና በቀጣይ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሥምምነት ላይ መደረሱን ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n



