ሰኞ ጥር 23 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 ግማሽ ዓመት 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን የገለጸ ሲሆን፣ በዚህም የእቅዱን 86 ነጥብ 4 በመቶ ማሳካት መቻሉን አስታውቋል።
ያለፈው ስድስት ወራት ለድርጅቱ አስቸጋሪ ወራት እንደነበሩ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም የስድስት ወራት እቅዱን ባቀደው ልክ ማሳካት ያልቻለው፣ የሰሜኑ ጦርነት በአገልግሎቱ ላይ ባስከተለው መስተጓጎል ነው ተብሏል።
በአማራ እና በአፋር ክልሎል ሙሉ በሙሉ ከአንድ ወር በላይ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ መቆየቱ በገቢው ላይ ተጽዕኖ መፍጠሩም ተገልጿል።
በጦርነቱ ምክንያት በአገልግሎት አሰጣጥ ማስተጓጎል ባይገጥመው የእቅዱን 97 ነጥብ 7 ማሳካት ይችል እንደነበር ፍሬሕይወት ጠቁመዋል።
በመርሻ ጥሩነህ
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n



