ሰኞ ጥር 23 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የአፍሪካ ህብረት በቡርኪና ፋሶ የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ አገሪቷ በማናቸውም የህብረቱ ጉዳዮች ላይ እንዳትሳተፍ አግዷል፡፡
ከሳምንት በፊት በሀገሪቱ የተካሄደው መፈንቅለ መንግስት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት የነበሩትን ሮህ ማርክ ካቦሬን ከስልጣን ማስወገዱን የሚታወስ ነው፡፡
እግዱ በአገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት እስኪከበር ድረስ የሚቀጥል እንደሚሆንም የአፍሪካ ህብረት አስታውቋል፡፡
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




