“ኑ የፈረሰውን የትውልድ ማፍሪያ ተቋም መልሰን እንገንባ” በሚል መሪ ሀሳብ ትምህርት ሚኒስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የገቢ ማሰባሰቢያ ሥምምነት ተፈራረሙ

0
375

ሐሙስ የካቲት 3 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ትምህርት ሚኒስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር “ኑ የፈረሰውን የትውልድ ማፍሪያ ተቋም መልሰን እንገንባ” በሚል መሪ ሀሳብ የገቢ ማሰባሰቢያ ለማዘጋጀት የሚያስችል ሥምምነት ተፈራርመዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እና የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ናቸው ሥምምነቱን የተፈራረሙት፡፡

የገቢ ማሰባሰቢያው ሙሉ በሙሉ የወደሙትን 1 ሺህ 90 ትምህርት ቤቶች ፣ 3 ዩኒቨርስቲዎች እና 3 ኮሌጆችን መልሶ ለመገንባት የሚውል መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

በዚህም መሠረት ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ አካላት ኢትዮ ቴሌኮም ያዘጋጃቸውን የክፍያ አይነቶች የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ይፋ አድርገዋል።

የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ማንኛውንም የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000448700945፣ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅም የፈቀደውን የብር መጠን ጽፎ ወደ 9222 በመላክ፣ በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥር 9222ን መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል።

በተጨማሪም በቴሌብር ዓለም አቀፍ ሀዋላ ከውጭ አገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም እንዲሁም የተለያዩ የትምህርት ግብዓቶችን 4 ኪሎ በሚገኘው የትምህርት ሚኒስቴር ዋናው መ/ ቤት በመምጣት ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻል የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here