ፍርድ ቤቱ የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የነአብዲ መሀመድ ኡመር አቤቱታን ውድቅ አደረገ

0
737

 

ሐሙስ የካቲት 3 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) አብዲ መሀመድን ጨምሮ 17 ተከሳሾች ከኛ ጋር ተከሰው የነበሩ ዕስረኞች ክስ ተቋርጦ እኛ ብቻ የምንታሰርበት ምንም ምክንያት የለም ። በህገመንግስቱ የተሰጠንን በእኩል የመታየት መብታችን የተነፈገ በመሆኑ ፍርድ ቤት አንቀርብም ሲሉ ተከሳሾቹ ባሳለፍነው ማክሰኞ አቤታታ ማሰማታቸው ይታወሳል።

በአቤቱታው ላይ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ትዛዝ ለመስጠት ለዛሬ በተያዘው ቀጠሮ ችሎቱ ተሰይሟል።

ሆኖም ዛሬ አብዲ መሀመድን ጨምሮ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙ 14 ተከሳሾች ችሎት አንቀርብም በማለት ሳይቀርቡ ቀርተዋል።

ነገር ግን በቂሉንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ ሙሴ እንድሪስ፣ ሼክ ሙክታር፣ ሼክ መሀመድ እና ሙስጠፋ ሀቢብ የተባሉ ሦስት ተከሳሾች በችሎት ቀርበው በአስገዳጅ ሁኔታ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ወደ ፍርድ ቤት እንዳመጣቸው አቤቱታ አቅርበዋል።

በተጨማሪም ከሌሎች ታራሚዎች ጋር ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲዛወሩ አንድ ላይ ጉዳያቸው እንዲታይላቸው ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱም የደረሰባቸው የመብት ጥሰት ካለ በጽሁፍ እንዲያቀርቡ አስተያየት ሰቷል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አብዲ መሀመድ ኡመር ጨምሮን አጠቃላይ ተከሳሾች ሌሎች ዕስረኞች ተፈተው እኛ ፍርድ ቤት የምንቀርብበት ምክንያት የለም ሲሉ ያቀረቡትን አቤቱታ በተመለከተ መርምሮ አቤቱታውን ማቅረብ ያለባቸው ክስ ላቋረጠው መንግስታዊ አካል እንጂ ለዚህ ችሎት አደለም። ጥያቄው የህግ መሰረት የሌለው ነው ሲል አቤቱታቸውን ውድቅ ማድረጉን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ዘግባለች።

ስለዚህ ፍርድ ቤቱ በያዘው ቀጠሮ የምስክር አሰማም ሂደት ይቀጥላል ሲል፣ የዓቃቢህግ ቀሪ ምስክርን ለመስማት ለየካቲት 14 ቀን 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።
የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዛሬ ያልቀረቡ 14 ተከሳሾችን በቀጣይ ቀጠሮ እንዲያቀርብም አዟል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here