አርብ የካቲት 4 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ይዞ እንደነበር ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት በትናንትናው ዕለት የጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ በመዋሉ ምክንያት በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ከንቲባ አዳነች አቤቤ መገኘት አለመቻላቸው ተገልጿል።
ቢሆንም ግን ከከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች መካከል በምክትል ከንቲባው የሚመራ የአመራር ቡድን በመንበረ ፓትሪያርኩ ፅ/ቤት ተገኝተው ከብፁአን የቋሚ ሲኖዶሱ አባላት ጋር በቀጣይ ወይይት ስለሚደርግበት ሁኔታ ምክክር ያደረጉ ሲሆን፤ ምክክሩም በመልካም ሁኔታ መካሄዱን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት በጋራ ሥምምነት ለሚቀጥለው ማክሰኞ የካቲት 8/ 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ በመያዝ በቅዱስ ሲኖዶሱ ፅ/ቤት ለመገናኘት በጋራ ተወስኖ ቀጠሮ መያዙም ታውቋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n






