አርብ የካቲት 4 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስድስት ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከአዲስ አበባ ምክር ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የሃይማኖትና የመንግስት ግንኙነትን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሰጡት ምላሽ፤-
👉ሃይማኖትና መንግስት የተለያዩ ናቸው፤ የሚኖራቸው ግንኙነት በህገ መንግስት በግልጽ ተቀምጧል፡፡
👉በሃይማኖት እያዳሉ አገር መምራት አይቻልም
👉የብልጽግና አመራር በየትኛውም ሃይማኖት ተቋም የወከለው ሰው የለውም፡፡
👉ግንኙነታችን ተቋማዊ ነው፤ በሰላምና በልማት ጉዳይ በትብብር እንሰራለን፡፡
👉የመንግስትን ድንበር ሳናልፍ ድጋፍ እናደርጋለን፤ በበአላት አከባበር ላይ ለአገር ገጽታ ግንባታ ጠቃሚ ስለሆነ እንደጋገፋለን፡፡
👉መንግስት ነጻነቱን ጠብቆ ስራውን እንዲያከናውን ሊጠበቅ ይገባል፤ ሃይማኖት ተቋማትም በነጻነት ኃይማኖታዊ ሥርዓታቸውን ማከናወን አለባቸው፡፡
👉ባለፉት 3 አመታት ከሃይማኖት ተቋማት ጋር ያለን ግንኙነት እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡
👉በኣላት በትብብር እንዲከበሩ ስንሰራ ቆይተን ውጤታማ ሆነናል::
👉የተለያዩ ሃይማኖት ተቋማት አገር ችግር ላይ ስትወድቅ አብረው ቆመው ፈጣሪን ለምነዋል::
👉የመረጠንን ህዝብ በማክበር ለሃይማኖት ተቋማት ድጋፋችንን ስናደርግ ቆይተናል::
👉ባለፉት 3 አመታት 2014ን ሳይጨምር ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ በአጠቃላይ 1 ሚሊዮን ካሬሜትር የሆነ 89 የቦታ ጥያቄዎችን አስተናግደናል
👉ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች 260 ሺህ 938 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው 85 ቦታዎችን አስተናግደናል
👉ለወንጌል አማኞች 98 ሺህ 290 ካሬሜትር የሆነ 47 የቦታ ጥያቄዎችን አስተናግደናል
👉ለ7ተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን 3 ቦታ በአጠቃላይ 6ሺ 812 ካሬ ሜትር የሆነ የቦታ ጥያቄዎችን አስተናግደናል
👉ለኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በአጠቃላይ 7700 ካሬሜትር ስፋት ያለው 3 የቦታ ጥያቄዎችን አስተናግደናል ሲሉ ምላሽ መስጠታቸውን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n





