በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በተከሰተው የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ13 ሰዎች ላይ ከባድ አደጋ መድረሱ ተገለፀ

0
1018

ሐሙስ የካቲት 10 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) መነሻውን ከሞያሌ ያቤሎ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ 65 ሰዉ ጪኖ ስጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኦሮ 34983 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በቆንጋ ቀበሌ ተገልብጦ በሰዉና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

በተከሰተው የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ13 ሰዎች ላይ ከባድ አደጋ ማድረሱን የይርጋጨፌ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ታምራት ምትኩ ገልጸዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በይርጋጨፌና በዲላ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የአደጋ መንሴ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን የዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል ።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here