Ethiopian Business Review (EBR) መጽሔት 104ተኛ ዕትም በገበያ ላይ ዋለ

0
1060

የአዲስ ማለዳ ጋዜጣ አሳታሚ የሆነው ቻምፒየን ኮሚውኒኬሽን የሚያሳትመው ወርሃዊው የቢዝነስ መጽሔት Ethiopian Business Review (EBR) 104ተኛ ዕትም በገበያ ላይ ዋለ።

በዚህ ዕትም በመንግሥት ከፍተኛ አመራር ላይ በወጣትነት ዕድሜ የሚገኙት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽነር ሌሊሴ ነሚ እንግዳ በመሆን፤ በተለይ በውጪ መዋዕለ ነዋይ ዘርፍ ፍሰት፣ ተግዳሮት፣ የአሰራር ማሻሻያዎች እና ቀጣይ እጣ ፈንታ ዙሪያ ሰፋ ያለ ቆይታ አድርገዋል።

ጉምቱው የሥራ ፈጣሪና ባለሀብት እንዲሁም የቀድሞው የኢትዮጵያና የአዲስ አበባ የንግድ ማኅበራት ምክር ቤቶች ፕሬዝዳንት ከሆኑት ብርሃነ መዋ ጋርም፤ በተለይ
ከዳያስፖራው የመዋዕለ ነዋይ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘና ራሳቸውም ወደ አገር ውስጥ ይዘውት ስለመጡት አማራጭና ሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት ከመጽሔቱ ጋር አድርገዋል።

ዳያስፖራው በኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ውስጥ ስለሚኖረው ሚና፣ ስለ ጤና መድኅን እና ሌሎች በርካታ ምጣኔ ሀብታዊ መጣጥፎችን እንዲሁም ማኅበራዊ ፋይዳ ያላቸው ጉዳዮች በሰፊው ተተንትነዋል። በተጨማሪም ወቅታዊ በሆኑና በተመረጡ ምጣኔ ሀብታዊና ማኅበረ- ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ታዋቂ ምሁራን ሰፊ ምልከታቸውን አጋርተዋል።

መጽሔቱን በከተማችን ውስጥ በሚገኙ ትላልቅ ሱፐርማርኬቶች እና በሁሉም የ‘ቡክወርልድ’ መደብሮች ያገኙታል፤ በመደበኛነት ያሉበት ድረስ እንዲደርዎትም የመጽሔታችን ቤተሰብ አባል እንዲሆኑም ጋብዘንዎታል።

ለማንኛውም መረጃ በ0961 41 41 41 ይደውሉ።
—————————
በተጨማሪም የEthiopian Business Review (EBR) የሶሻል ሚዲያዎችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
website: https://bit.ly/3uYFG8m
Telegram: https://bit.ly/3Haic2J
Facebook: https://bit.ly/3oWSbxh
Twitter: https://bit.ly/3GQZWLq
LinkedIn: https://bit.ly/3JzEJHH

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here