ሐሙስ የካቲት 10 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) መነሻውን ከሞያሌ ያቤሎ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ 65 ሰዉ ጪኖ ስጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኦሮ 34983 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በቆንጋ ቀበሌ ተገልብጦ በሰዉና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።
በተከሰተው የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ13 ሰዎች ላይ ከባድ አደጋ ማድረሱን የይርጋጨፌ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ታምራት ምትኩ ገልጸዋል።
ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በይርጋጨፌና በዲላ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የአደጋ መንሴ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን የዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል ።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n





