በአለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ዋና ዳይሬክተር የተመራ ልዑክ ጅግጅጋ ከተማ ገብቷል

0
877
አርብ የካቲት 11 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ዋና ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን የተመራ ልዑክ ሶማሊ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገብቷል።
 
ሉዑካን ቡድኑን የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ ሙሁመድ፣ የሶማሊ ክልል ም/ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ኡስማንና ከፍተኛ የክልሉ የሥራ ሀላፊዎች በጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል ኤርፖርት በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
 
በአለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን ዋና ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን የተመራውን የልዑካን ቡድን በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ዙሪያም ከክልሉ ፕሬዚዳንትና ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎም ይጠበቃል ሲል የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ዘግቧል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here