አርብ የካቲት 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ፖላንድ ድንበር አቋርጠው እንዲገቡ በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳሰበ።
በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ኢትዮጵያውያን ችግር እንዳይገጥማቸው ክትትል እያደረገ መሆኑን ኤምባሲው ገልጿል።
በዚህም በዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ፖላንድ ድንበር አቋርጠው መግባት እንዲችሉ ከፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ተነጋግሮ ማስፈቀዱን አስታውቋል።
በመሆኑም በታቸለ ፍጥነት በዩኩሬን የሚኖሩ እና ወደ ድንበር ጉዞ በማድረግ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ፖላንድ ግዛት በመግባት ወደ ኢትዮጵያ በተቻለ ፍጥነት እንዲጓዙ አሳስቧል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n



