“የገጠመንን ሰፊና ውስብስብ ጦርነት በአሸናፊነት ለመወጣት የመረጃ ሚና ከፍተኛ ነበር።” ምክትል ጠ/ኤታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ

0
1058

አርብ የካቲት 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) “የገጠመንን ሰፊና ውስብስብ ጦርነት በአሸናፊነት ለመወጣት የመረጃ ሚና ከፍተኛ ነበር::” ሲሉ የኢፌዴሪ ምክትል ጠ/ኤታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ ገለጹ፡፡

የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ የዕውቅና እና የምስጋና ዝግጅት ላይ የተገኙት የመከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠ/ኤታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ ፣ ሳናውቀው አብሮን ኖሮ የነበረው ጠላት የከፈተብንን ጥቃት ከዜሮ በመነሳት ለመመከት የዋና መምሪያው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ምስጋና እንደሚገባው ገልፀዋል።

አገራችን ያጋጠማትን ጦርነት በከፍተኛ እልህና ጥረት በመረጃ በማገዝ የተገኘውን ውጤት ለማስቀጠል በቴክኖሎጂና በብቁ የሰው ሀይል በመታገዝ ለሚሰጣቸው ግዳጅ ዝግጁነታቸውን የበለጠ ማረጋገጥ እንደሚኖርባቸውና፤ ለዚህም ተቋሙ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጄኔራል አበባው አረጋግጠዋል።

የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌ/ጀነራል ብርሀኑ በቀለ፣ ዋና መምሪያው በሰላምም ሆነ በጦርነት ወቅት በሰራቸው ሥራዎች የአገራችንን ውስጣዊም ሆነ የውጭ ጠላቶችን የትርምስና አገር የማፍረስ ሴራ እንዳይሳካ ማስቻሉን ገልፀዋል።

በሥራ አፈፃፀማቸውና የመቆያ ጊዜያቸውን በመሸፈን የተሾሙና የተሸለሙ አባላትም ሽልማቱ በቀጣይ ለሚሰጣቸው ግዳጅ ተነሳሽነትን የሚፈጥር በመሆኑ ለላቀ የግዳጅ አፈፃፀም ዝግጁ እንዲሆኑም አሳስበዋል።

በዕለቱ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፤ የመከላከያ የሙዚቃ ኦርኬስትራ አገራዊ ዜማዎች በማቅረብ ድምቀት መስጠቱን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here