አርብ የካቲት 25 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ መጋቢት 4 ቀን 2014 እንደሚፈጸም ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ፤ አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ መጋቢት 4 ቀን 2014 በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዲከናወን ውሳኔ ማሳለፉን የቤተክርስቲያኒቱ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት አስታውቋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




