“ዛሬ የምንጽፈው ዜና እውነት ካልሆነ ታሪክ ይዛባና ትውልድ ያባላል”:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

0
564

አርብ የካቲት 25 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን የ80 ዓመታት ጉዞ ላይ በሚያተኩረው ፓናል ውይይት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ አንጋፋ ቋማትን ስንዘክር ዘላቂና አገር አሻጋሪ ተቋማትን ለመፍጠርና ለማጠናከር ወሳኝ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

የዛሬ ዜና የነገ ታሪክ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዛሬ የምንጽፈው ዜና እውነትን ያዘለ ካልሆነ ነገ ታሪክ ይዛባና ትውልድን የሚያባላ ይሆናል ብለዋል።

አንጋፋ የሆነው ኢዜአ ዋና ግቡ እውነትንና የአገር ጥቅምን አስተሳሰሮ መሄድ ሊሆን ይገባልም ብለዋል።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ ኢዜአ ሲመሰረት ብዙዎቹ የአፍሪካ አገራት ራሳቸውን ማስተዳደር እንኳን አልጀመሩም። ተቋሙ ያለውን የረጅም ዓመታት ልምድ ልምድና የሰው ሀብት በመጠቀም ለአገር ጥቅም መጠበቅ በትኩረት እንዲሠራ መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

የኢዜአ 80ኛ ዓመት በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለትም ዓውደ ርእይ የተከፈተ ሲሆን የፓናል ውይይትም ይካሄዳል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here