የደብረ ብርሀን ከተማ ምክትል ከንቲባ ደስታ አንዳርጌ በቁጥጥር ስር ዋሉ

Views: 340

የደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ደስታ አንዳርጌን ጨምሮ አራት ባለሙያዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከከተማ መሬት ጋር በተያያዘ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው እንደሆነ የከተማው ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኮማንደር ታዬ ወልደጊዮርጊስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል።

ከምክትል ከንቲባው ደስታ አንዳርጌ በተጨማሪም የከተማው የመሬት ልማት ቡድን መሪ ደምሴ ተፈረደኝ እና ኃይሉ ሽፈራው እንዲሁም ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በመግለጽ አመራሮቹ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል።

 

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com