ለወራት ዝግ የነበረው የመተማ -ገላባት መንገድ ክፍት ተደረገ

0
457

ለወራት ዝግ የነበረው የመተማ-ገላባት መንገድ ክፍት ኾኖ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ተጀመረ።
በአሸባሪነት የተፈረጀው የሕወሓት ወራሪ ኃይል በከፈተው ጦርነት ምክንያት ለ7 ወራት ተቋርጦ የነበረው የመተማ -ገላባት መንገድ ክፍት ኾኖ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ተጀምሯል ተብሏል።
በኹለቱም አገራት በኩል ያሉ የሚመለከታቸው አካላት፣ በቀጣናው የሚስተዋሉ ወንጀሎችን ለማስቆምና አካባቢውን ፍጹም ሠላማዊ ለማድረግ በጋራ እንደሚሠሩና፣ የንግድ ትስስራቸውንም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡
ለጋራ ደኅንነት የመረጃ ልውውጥና የጋራ ቅኝት ማድረግ እንደሚገባና በአገራቱ መካከል የቆየውን መልካም ግንኙነት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡ የሚያጋጥሙንን ችግሮች በጋራ ውይይት ለመፍታት፣ እንዲሁም ጽንፈኛውን የቅማንት ታጣቂ ቡድን እና አሸባሪውን የሕወሓት ቡድን በጋራ ለመዋጋት፣ ጥቆማ፣ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ እንደሚሠራ ተመላክቷል፡፡
መንገዱ ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ የንግድ ዕቃዎችን ማስገባትና ማስወጣት እንደሚቻል የተገለጸ ሲሆን፣ ሕብረተሰቡ ከጠዋቱ 1:00 ስዓት እስከ 11:30 እንዲንቀሳቀስም የስዓት ገደብ ተጥሏል ነው የተባለው።


ቅጽ 4 ቁጥር 174 የካቲት 26 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here