“ሲቄ” የሚለው የኦሮምኛ ቃል ‹አለንጋ› የሚል ትርጉም አለው። በገዳ ትውፊታዊ አስተዳደር ውስጥ በባሏ ጥቃት የደረሰባት ሚስት፣ ከሌሎች ሴቶች ጋር በመሆን ባሏ ላይ የካሣ ውሳኔ የምታሳልፍበት ስርዓት ሲቄ ይባላል።
ስለዕድሜ እና ትዳር ሲነሳ ሴት ልጅ እንደማትወድ የሚነገር ሓሳብ አለ። በአገራችን ባህል መሠረት ሴት ልጅ ገና ከመጀመሪያው ጀምሮ ጫና የሚበዛባት እና ኃላፊነት የሚሠጣት ስለሆነች፣ አደግ ማለት እንደጀመረች ቶሎ እንድታገባ ይፈለጋል። የውስጧን ፍላጎት ሳያውቅ ዘመድ አዘማዱ እና ቤተሰቦቿ ቶሎ እንድታገባ ይገፏፏታል ።
የተማረ ያልተማረውም በዚህ ጉዳይ ተመሳሳይ ነው የሚያስበው ማለት ይቻላል። አንድ ሴት፣ በተለይ ደግሞ ለአቅመ ሔዋን የደረሰች ወጣት፣ ወደትዳር እንድትገባ ለማሳመን ጥረት ሲደረግ ብዙ ጊዜ ይታያል። ከቤተሰብ ጀምሮ፣ “አግቢ እንጂ ቆመሽ ልትቀሪ ነው፣ ሳታገቢ ዕድሜሽ አለፈ” እየተባለች በቅርብ ጓደኛም ይሁን በቤተሰብ ዘንድ ትችት ሲደርስባት ይሰተዋላል። እሷ ግን የምትባለውን ነገር ማድረግ ወይም መፈጸም ሳትፈልግ ቀርታ ሳይሆን፣ የምታስቀድማቸው ነገሮች ስላሉና ሕይወት እንደምታሰበው ቀላል አልሆንላት ብሎ ሊሆን እንደሚችል መረዳት ያስፈልጋል።
ከዛ ይልቅ ግን፣ ለምን ይሆን ለመቆየት የፈለገችው? ችግር ገጥሟት ይሆን? የፈለገችውን ዓይነት የትዳር አጋር አጥታ ይሆን? ብሎ ማሰብ እና በተቻለ መጠን ውስጧን ለመረዳት መሞከር ጥሩ ነው። አስተያየት ከመስጠት በፊት ምን ዓይነት ስሜት እየተሠማት እንደሆነ ለመረዳት መቻል አለብን። ከሴት ልጅ ዕድሜ እና ከማግባት ጋር ተያይዞ ብዙ የምንታዘባቸው ነገሮች አሉ። ተማረችም አልተማረችም ቶሎ እንድታገባ በተለያዩ አጋጣሚዎች ጫና ሲደርስባት ማየት እየተለመደ ነው።
ለምንድን ነው እንደፍላጎቷ እንድትማር እና እራሷን እንዳትለውጥ የሚደረገው? ለምን በራሱዋ ፍላጎት የፈለገችውን ሠው በፈለገችበት ጊዜ እንድታገባ ዝም አትባልም? በሕብረተሰባችን ልማዳዊ አስተሳሰብ ውስጥ ከትምህርት ወይም እራስን ከመቀየር ይልቅ በአብዛኛው የሴት ልጅ ትዳር የበለጠ ዋጋ የሚሠጠው ለምንድነው? ለምን አታገቢም እያሉ ባገኙት አጋጣሚ ከመጠየቅ፣ እንዴት እስከ ዛሬ አላገባሽም? ቶሎ አግቢ እንጅ! ብሎ በመጠየቅ እንድትሸማቀቅ እና እንድትሳቀቅ ማድረግ ተገቢ አይደለም።
በዚህ በሠለጠነ ዘመን እየኖርን አሁንም ድረስ ከሴት ልጅ ዕድሜ ጋር ተያይዞ የሚነገሩ ግምገማዎች መቆም አለባቸው። የተደጋገመ አስተያየት በምትሰማበት ጊዜ ሴቷ ሳታምንበት እንድትወስን እና በራስ መተማመን እንዳይኖራት ሊያደርጋት ይችላል ። ይሄ ደግሞ በችኮላ እንድትወስን እና ደስታ የሌለው ጋብቻ እንድትመሠርት ሊያደርጋት ይችላል። ውሳኔውም ሴቷ በመንፈስም ሆነ በአካል ብቁ እንዳትሆን፣ እንዲሁም ዓላማዋን እንዳትፈልግ እና ተግባራዊ እንዳታደርግ ትልቅ ተጽዕኖ ያሳድርባታል።
የሠውን ምክንያት ሳናውቅ እና ሳንረዳ መፍረድ ተገቢ አይሆንም። ለምን አታገቢም የሚልን ጥያቄ ትተን ፍላጎቷን ለመረዳት እንሞክር። ከልማዳዊ አስተሳሰብ ውስጥ ወጥተን እንደሠለጠነ ሠው ማሰብ መቻል አለብን። ከቤተሠብ ጀምሮ ኹሉም የማኅበረሠብ ክፍል ከጎጅ ባህል እና ወግ ወጥቶ
ቅጽ 4 ቁጥር 174 የካቲት 26 2014


