የብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ሊቀ ጳጳስ የሽኝት መርሐ ግብር እየተከናወነ ነው

0
1420

ዕረቡ የካቲት 30 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ሊቀ ጳጳስ የሽኝት መርሐ ግብር በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመከናወን ላይ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና የብፁዕነታቸው ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል።

የብፁዕነታቸው ሥርዓተ ቀብር ነገ መጋቢት 1 ቀን 2014 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ካህናትና ምዕመናን በተገኙበት በደብረ ብርሃን ከተማ በምትገኘው በጥንታዊቷ የደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ይፈጸማል ሲል የኢኦተቤ ቴቪ ዘግቧል።

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትን ከ30 ዓመታት በላይ የመሩት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው የካቲት 27 ቀን 2014 በ97 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው የሚታወስ ነው።

ፎቶ:- ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
______________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here