በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁ ተገለፀ

0
568

ሐሙስ መጋቢት 1 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ሲካሄድ የቆየው የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ እስር ቤቶችና ካምፖች በፈታኝ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለመመለስ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡

የዜጎቹን ማንነት፤ ያሉበትንሁኔታና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ለማጠናቀር ወደ ሥፍራው አቅንቶ የነበረው ልዑክ መመለሱን ያወሱት ቃል አቀባዩ፤ ዜጎቹን መመለስ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡

ለተልዕኮው ስኬትም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሚመራ 16 ተቋማትን ያካተተ ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተለው ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡

በተያያዘም ዩክሬንና ሩሲያ በመካከላቸው የተፋፋመው ግጭትና ውጊያ በማቆም ዓለም ጎራ ለይቶ እንዲዋጋ ከሚያነሳሱ ትንኮሳዎች እንዲቆጠቡ ኢትዮጵያ ጥሪ ማቅረቧን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል፡፡

በሁለቱ አገራት መካከል የተካረረው ሁኔታ ዓለምን በጎራ ወደ ውጊያ እንዳያስገባ ተንኳሽ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ችግሩ የንግግር መፍትሄ እንዲበጅለት ኢትዮጵያ ፅኑ አቋም አላት ሲሉ አምባሳደር ዲና መግለፃቸውን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያንፀባረቀችው ድምፅ አልባ ውሳኔም የዚሁ ማሳያ ነው ሲሉም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡

_________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here