ሐሙስ መጋቢት 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በሳዑዲ የሚገኙ 35 ሺህ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ መመዝገባቸውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።
አምባሳደር ዲና በዛሬው ዕለት ሳምንታዊ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሥራ ማብራሪያ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በሳዑዲ አረቢያ ከ100 ሺህ በላይ ኢትዮጲያውያን ዜጎች እንዳሉ አንስተው እነዚህን ዜጎች ወደ አገራቸው ለመመለስ ከሳዑዲ መንግስት ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅትም 35 ሺህ ዜጎች ወደ አገራቸው ለመመለስ ምዝገባ መከናወኑን አምባሳደሩ መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ ዘግቧል።
በቀጣዮቹ ቀናት ወደ አገራቸው መመለስ ያለባቸውን ዜጎች ከሳዑዲ የማስወጣት ሥራው እንደሚጀምርም አምባሳደር ዲና ተናግረዋል። ወደ አገራቸው የሚመለሱ ዜጎችን እያጣሩ የመመዝገብ ሥራ ቀጣይነት እንዳለውም አስረድተዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4



