የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ በጦርነት የወደሙና የፈራረሱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ አስታወቀ

0
723

ሐሙስ መጋቢት 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA) በጦርነት የወደሙና የፈራረሱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA) የኢትዮጵያ ዋና ተወካይ ዶ/ር ካትሱኪ ሞሪሀራ ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ ኤጀንሲው በትምህርት ዘርፍ ለኢትዮጵያ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ የወደሙ ትምህርት ቤቶች ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፍም ጠይቀዋል።

የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA) የኢትዮጵያ ዋና ተወካይ ካትሱኪ ሞሪሀራ ከ2006 እስከ 2020 እ.ኤ.አ ከ290 ሚሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ እንደተደረገና ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶችን መገንባት መቻሉን ተናግረዋል።

በጦርነት የወደሙና የፈራረሱ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ተቋማቸው የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ ያረጋገጡት ተወካዩ ለትምህርት ቤቶች ከሂሳብና ሳይንስ ትምህርት ጋር በተያያዘ የሚያስፈልጉ የቤተ-ሙከራ ግብዓቶችንና ቁሳቆሶችን እንደሚያሟሉ ገልፀዋል፡፡

የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ከ2003 እስከ 2021 እ.ኤ.አ ድረስ በኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here