ኢትዮጵያ በኮቪድ19 ምክንያት ድንበሮቿን ዘጋች

Views: 178

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኮቪድ19 ስርጭትን ለመግታት ሁሉም የአገሪቱ ድንበሮች ለሰዎች ዝውውር ዝግ መደረጋቸውን ገለጹ።

የድንበር መዘጋቱ የሎጅስቲክስ አቅርቦት ለማዳረስ የሚደረገውን ጥረት እንደማያካትት የገለጹት ዐቢይ አሕመድ

በዛሬው እለት መጋቢት 14/2012 የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በተገመገሙበት ዕለት ማህበረሰቡ ከንክኪ ተራርቆ እንዲንቀሳቀስ የተላለፈው መልዕክት ባለፉት ቀናት በአግባቡ እየተፈጸመ አይደለም ተብሏል።

 

ቅዳሜ እና እሁድ በነበረው የእምነት ተቋማት መርሃ ግብሮች ላይም በቂ የመከላከል እርምጃ እንዳልተወሰደ የተገመገመ ሲሆን  የሃይማኖት አባቶች በቀጣይ ምዕመኖቻቸውን ከማስተማር ባለፈ በተግባር እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ምንጭ ፋና

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com