ሐሙስ መጋቢት 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የቀድሞ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዡር ሹም ሳሞራ የኑስ ለእነ ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው በመከላከያ ምስክርነት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ቀረቡ።
የቀድሞ የሜቴክ ዋና ዳሪክተር እነ ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው በቀረበባቸው የዕርሻ መሳሪያ ግዢ ክስ በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ መጥሪያ እንዲደርሳቸ ከተዘረዘሩት ምስክሮች መካከል የጦርሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዡር ሹም ሳሞራ የኑስ አንዱ ናቸው።
ሳሞራ የኑስ ችሎት የቀረቡ ቢሆንም የሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው የኮነሬል ሙሉ ገ/እ እና የሌ/ኮ ተከስተ ሀ/ማ ጠበቃ ሀፍቶም በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ የለኝም ስላሉ ምስክርነታቸው ይታለፍልን ብሏል።
በዚህም የቀድሞ ጠቅላይ ኢታማዡር ሰሞራ የኑስ ምስክርነታቸው ሳይሰማ መቅረቱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።
ነገር ግን ሳሞራ የኑስ በነ ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ላይ በቀረበው ሌላኛው የራዳር ግዢ ክስን በተመለከተ በመከላከያ ምስክርነት ለመጋቢት 14 እንዲቀርቡ መጥሪያ እንደደረሳቸው ተገልጿል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4na




