የጨፌ ኦሮሚያ አንደኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ 6ኛ የሥራ ዘመን ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል

0
606

ሰኞ መጋቢት 12 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የጨፌ ኦሮሚያ አንደኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ 6ኛ የሥራ ዘመን ጉባኤ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት አፈ ጉባኤዋ ሰዓዳ አብዱራህማን ጨፌው ባለፉት ሰባት ወራት በርካታ ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

የጨፌውንና የመንግስት አካላትን የማስፈፀም አቅም ጠንካራ ለማድረግ የክትትልና የግምገማ ሥርዓቱን ጠንካራ በማድረግ የማህበረሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በተገቢው መንገድ ምላሽ እንዲያገኝ በማድረግ ረገድ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱንም ገልፀዋል፡፡

እንደ ክልል ያጋጠመውን ድርቅ ለመከላከልና አስከፊ ጉዳት ሳያደርስ በህዝቡ የመረዳዳት ባህል ችግሩን ከመቅረፍ ጎን ለጎን የክልሉ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ለጨፌው አባላት አስረድተዋል፡፡

ጨፌው ከህዝቡ የተሰጠውን ተልዕኮ መሰረት በማድረግ የህዝቡን ችግር እስከ ታችኛው መዋቅር በመድረስ ማህበረሰቡን ችግርና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመመለስ እየተሰራ እንደሚገኝ መናገራቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም አፈ ጉባኤዋ የክልሉን ሰላም ለማወክ የሚጥሩ ቡድኖችን ከመከላከል አንፀር እና ከክልሉ ከመሰረታቸውን ለማጥፋት የክልሉ መንግስት ትኩረት በመስጠት በሰራው ተግባር ለውጦች እየታዩ መምጣታቸውን አንስተዋል፡፡

ጨፌው ዛሬና ነገ የአስፈፃሚው አካላትን የሰባት ወራት የሥራ አፈፃፀም ይመለከታል። የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችንና ደንቦችን በማየትና በመገምገም ውሳኔ የሚያስተላልፍ ሲሆን፤ የተለያዩ ሹመቶችን በማየት የሚያፀድቅ መሆኑም ታውቋል፡፡

_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here