ሰኞ መጋቢት 12 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደቡብ ሱዳን የሰላም ማስከበር ተልእኮ ላይ የተሰማሩ የፌደራልና የክልል ፖሊስ አመራሮች ለአንድ ዓመት ያህል ላበረከቱት አስተዋፅኦ ሜዳሊያ ተበረከተላቸው፡፡
በሜዳሊያ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይ በመገኘት ሜዳሊያውን የሰጡት ረ/ኮሚሽነር መኮንን አሻግሬ እና ረ/ኮሚሽነር ፋሲል አሻግሬ ናቸው፡፡
ሰላም አስከባሪ አመራሮቹ አገራቸው ኢትዮጵያን ወክለው በተመደቡበት የግዳጅ ቦታዎች ሁሉ ኃላፊነታቸውን በብቃት በመወጣት አኩሪ ተግባር በመፈጸማቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል ረ/ኮሚሽነሮቹ፡፡
አገራችን ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ተልእኮ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም መሆኗን ገልጸው ሠራዊቷ ለግዳጅ አፈፃፀም በተመደበበት አገራት ሁሉ አድናቆት ማትረፉን ተናግረዋል።
ይህ ለእኛም ሆነ ለተቋማችን ታላቅ ክብርና ኩራት ነው ካሉ በኋላም፤ በቀጣይም አመራሮቹ በሚሰማሩባቸው የሥራ መስኮች ሁሉ ተግባራቸውን በብቃትና በትጋት በተመሳሳይ እንዲወጡ በራሳቸውና በኢትዮጵያ ፌደራል ፓሊስ ሥም ከአደራ ጭምር አሳስበዋል።
ረ/ኮሚሽነሮቹ ለተሸላሚ አመራሮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸውንም የፌዴራል ፓሊስ አስታውቋል።
____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




