የፈረንሳይ መንግስት ለቅርስ ጥገናው የገባውን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ ግብዓቶችን ወደ አገር ውስጥ እያስገባ መሆኑ ተገለፀ

0
784

ሰኞ መጋቢት 12 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የፈረንሳይ መንግስት ለላሊበላ ውቅር አቢያተ ክርስቲያናት ጥገና የገባውን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ ግብዓቶችን ወደ አገር ውስጥ እያስገባ መሆኑን የላሊበላ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በኮሮና ቫይረስ መከሰትና በጦርነቱ ምክንያት ለላሊበላ ውቅር አቢያተ ክርስቲያናት በፈረንሳይ መንግስት ሊደረግ የነበረው እድሳት ለረጅም ጊዜ መቋረጡ ይታወሳል፡፡

የላሊበላ ከተማ የባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ መሪ ጌታ መልካሙ አለሙ ለአሀዱ እንደተናገሩት ለውቅር አቢያተ ክርስቲያኑ 24 የተለዩ ቦታዎች ላይ የቅድመ ጥገና ሥራ ለመስራት አስፈላጊ ቁሳቁሶች እየገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በሚደረገው ጥገና ዙሪያ ከማህበረሰቡ ጋር ምክክር መደረጉን የተናገሩት ኃላፊው የቀድሞ ይዘቱን ሳይለቅ በአገር በቀል ቁሳቁሶችና ግብዓቶች እንዲጠገን ሥምምነት ላይ መደረሱን ገልጸዋል፡፡

የቅድመ ጥገናው አንገብጋቢ ችግሮችን ቅድሚያ መፍትሄ በመስጠት የሚጀመር ሲሆን፤ ዋናው የጥገና ሥራም ጎን ለጎን ተግባራዊ እንደሚደረግ እና አሁን ላይ ከውጪና ከአገር ውስጥ የተውጣጡ አዲስ የሙያው አማካሪዎች ተቋቁመው አንጻራዊ ሰላም በመኖሩ እንቅስቃሴው መጀመሩን ተናግረዋል ሲል አሀዱ በዘገባው አመላክቷል፡፡

በላሊበላ ከተማ ማህበረሰቡ አሁን ላይ ሰላማዊ እንቅስቃሴውን የመጀመረ ቢሆንም የውሀ፤ የኤሌትሪክ ሀይል፤ የኑሮ ውድነት ፈተና ሆኖበታል የሚሉት ኃላፊው፤ በከተማው ለሚደረገው የቅርስ ጥገናም ሆነ የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት የክልልና የፌደራል መንግስቱ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here