ዕረቡ መጋቢት 21 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የፊንቴክስ 3ኛ ዙር የፈርኒቸር፣ የቤተ ውበትና የግንባታ አጨራረስ ምርቶች አገልግሎቶች እና ቴክኖሎጅዎች ዓለም ዓቀፍ አውደ ርዕይና ኮንፍረንስ ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 1/2014 ድረስ በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል፡፡
ዓለም ዓቀፍ አውደ ርዕይና ኮንፍረንሱ “ንግድዎን በመቅረዝ ላይ ያኑሩ” በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ፕራና ኤቨንትስ እና አፍሪካን ትሬድ ፖርትረንስ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
በአውደ ርዕዩ ለፈርኒቸር አምራቾች ዘላቂ የንግድ ትስስርን ከመፍጠር እና የዘርፉን እድገት ማረጋገጥ በሚያስችል ሁኔታ፤ የንግዱን ማኅበረሰብ ትኩረት በመሳብ ለግብይት ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል ተብሏል፡፡
በዘርፉ ላይ የሚደረገው የውይይት መድረክ ለፖሊስ አውጭዎች፣ ለንግዱ ማኅበረሰብ እና ለባለሙያዎች ዘላቂ ልማት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግም ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ በዘርፉ ለምታካሂደው የምጣኔ ሀብት ልማት የአቅም ግንባታ መፍጠር የሚያስችል ትምህርትና ስልጣና፣ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ተሞክሮዎች ከተለያዩ አገራት በተውጣጡ ባለሙያዎች እንደሚቀርብ ተጠቁሟል፡፡
በአውደ ርዕዩ ላይ ከ60 በላይ ኩባንያዎች ከአገር ውስጥ፣ ከኬኒያ፣ ከፖላንድ እና ከቱርክ የሚሳተፉ ሲሆን፣ ከ400 በላይ ገዥዎችና ከ4 ሺሕ በላይ የንግድ ማኅበረሰብ አባላትና ጎብኚዎች እንደሚስተናገዱ ይጠበቃል፡፡
በኢትዮጵያ በፈርኒቸር ምርት ላይ ለተሰማሩ ለዘርፉ አምራቾች የተሰጠው ትኩረት አናሳ መሆኑና፤ ዘርፉ በሚፈለገው ልክ አለማደጉን የፈርኒቸር አምራቾች ማኅበር ገልጻል፡፡
የአገር ውስጥ ፈርኒቸር አምራቾችን ማበረታት እንደሚገባ እና ኢትዮጵያ ከውጭ ፈርኒቸር የሚታገባበትን የውጭ ምንዛሬ ማዳን እንዲሚገባም በመድረኩ ተጠቁሟል፡፡
በመርሻ ጥሩነህ
____
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n



