“መንግስት በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ሥራውን ሙሉ በሙሉ ጀምሯል”፦ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

0
890

ዕረቡ መጋቢት 21 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) መንግስት በሳውዲ አረቢያ በአሰቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገር ቤት የመመለስ ሥራውን ሙሉ በሙሉ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሚፍቲ ገለጹ።

ቃል አቀባዩ ዛሬ ጧት በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከሳውዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ለማስመልስ ሰፊ ሥራ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።

በዛሬው ዕለትም በሳውዲ የሚገኙ ዜጎችን ለመመለስ የቅድመ ምዝገባ ሥራ ሰርቶ ሙሉ ለሙሉ የመመለስ ሥራውን ተጀምሯል ብለዋል።

ከስደት ተመላሾቹ ጊዜያዊ መጠለያ የሚያርፉ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ፤ በቀጣይነት የሚቋቋሙበት መንገድ ይሰራል ሲሉ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ማስታወቃቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ከሳዑዲ ተመላሽ ዜጎችን ለመመለስ መንግስት በሚያደርገው ጥረት ከ7 እስከ 11 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎችን ለመመለስ እቅድ መያዙ ይታወቃል፡፡

ዛሬ ማለዳም በመጀመሪያው በረራ ከሪያድ 157 ህጻናትና 341 ሴቶች በድምሩ 498 ዜጎች ወደ አገራቸው ገብተዋል።
________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here