በአፋር ክልል በጊዜያዊነት ትምህርት ለማስቀጠል ድንኳኖች መሰራጨታቸው ተገለፀ

0
914

ሐሙስ መጋቢት 22 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአፋር ክልል በጦርነት የተፈናቀሉ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት ትምህርት ለማስጀመር 38 ድንኳኖች ለወረዳዎች ማከፋፈሉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን መሪ ዑመር መሀመድ እንደገለጹት፤ ድንኳኖቹ የተሰራጩት በጦርነት ተፈናቅለው የመጡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በጊዚያዊነት እንዲጀምሩ ለማስቻል ነው።

ለወረዳዎቹ በተከፋፈሉት ድንኳኖች በጦርነቱ አዲስ ተፈናቅለው የመጡ ተማሪዎችና ትምህርት ቤቶቻቸው በተፈናቃዮች መጠለያነት የተያዙባቸው ተማሪዎች በጊዜያዊነት ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉባቸው እንደሚደረግ ቡድን መሪው ተናግረዋል፡፡

በድንኳኖቹም በጊዚያዊነት ከ 3 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል።

የተሰራጨው ድንኳን ከተፈናቀሉ ተማሪዎች ቁጥር አንጻር በቂ ባለመሆናቸው ተጨማሪ ድንኳኖች እንዲፈለጉ ጥያቄ መቅረቡም ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ክልሉ ላይ በነበረው ጦርነት ምክንያት 65 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ይታወሳል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here