ሐሙስ መጋቢት 22 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የተለያዩ ችግር ደርሶባቸው በቤሩት የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር መጠለያ የነበሩ እና ያለህጋዊ ሰነድ ይኖሩ የነበሩ 36 ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር አስታወቀ።
በቤይሩት የኢፌዲሪ ቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤት ከሊባኖስ የመንግስት አካላት እና ELMA ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር 4 ህጻናትን ጨምሮ 36 ዜጎቻችን ወደ አገራቸው እንዲሸኙ ማድረጉን ቆንስላ ጀኔራል ጽ/ቤቱ ገልጿል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




