በአሰላና ኢተያ አካባቢ የዕንፋሎት ኃይል ማመንጫ ግንባታ ለማከናወን የ100 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈረመ

0
475

በኢትዮጵያ በአሰላና ኢተያ አካባቢ የ50 ሜጋ ዋት የዕንፋሎት ኃይል ማመንጫ ግንባታ ለማከናወን የ100 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ተፈረመ።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የቱሉ ሞዬ አገር በቀል ድርጅትና ሚትስቡሽ ኮርፖሬሽን ሲሆኑ፣ ፕሮጀክቱ የሚከናወነው ከፈረንሳይ መንግሥት በተገኘ ገንዘብ ነው ተብሏል።
ከዕንፋሎት የሚገኝ የኃይል አማራጭ ከአካባቢ ብክለት የፀዳና ዘላቂ በመሆኑ ተፈላጊነቱ ከፍተኛ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም በዘርፉ ዕምቅ ኃይል ስላላት ማልማት እንደሚገባ ተመላክቷል።
ለዘርፉም መንግሥት ቀጣዩን 10 ዓመት የሚያገለግል ፖሊሲ ቀርፆ ወደ ሥራ መግባቱ ተመላክቷል። በኃይል አቅርቦት ዘርፉ ላይ የግል ዘርፉ እንዲሳተፍ እንደሚፈለግና በዚህም መንግሥት ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑ ነው ተያይዞ የተገለጸው።


ቅጽ 4 ቁጥር 178 መጋቢት 24 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here