ከቤት ውጭ አየር በአግባቡ በሚዘዋወርባቸው ቦታዎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግን የሚያስገድድው መመሪያ ቀሪ ተደረገ

0
877

አርብ መጋቢት 23 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከቤት ውጭ አየር በአግባቡ በሚዘዋወርባቸው ቦታዎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግን የሚያስገድድው መመሪያ ቀሪ መደረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተሻሽሎ የወጣው መመሪያ ቁጥር 882/2014 አስመልክቶ የጤና ሚንስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የወረርሽኙን አሁናዊ የስርጭት ደረጃ እና ክትባት በስፋት መገኘትን ታሳቢ በማድረግ፤ የተወሰኑ ክልከላዎችና ግዴታዎችን በማላላት ወይም በማስቀረት ይበልጥ ዉጤታማ የሚሆን የጥንቃቄ እርምጃዎችንና ክትባትን ትኩረት የሚያደርግ አዲስ መመሪያ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ተሻሽሎ በወጣው መመሪያ መሰረትም:- ከቤት ውጭ አየር በአግባቡ በሚዘዋወርባቸው ቦታዎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ የማድረግ ግዴታ ቀሪ ተደርጎል።

በቤት ዉስጥ ወይም ድንኳን በመሳሰሉ በተከለለ ሁኔታ ከሚደረጉ ውጭ በሚደረጉ መሰባሰቦች ላይ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ አይሆንም መባሉን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል።

ስብሰባን በተመለከተ አዳራሹ መያዝ በሚችለው ልክ ሆኖም ግን ክትባት እና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ እንዲሁም ርቀታቸውን በመጠበቅ የሚደረግ ይሆናል።

ማንኛውም ተቋም ወይም የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ አካል አገልግሎቱን በሚሰጥበት ጊዜ ሰራተኛው እና ተገልጋዩ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ የማስደረግ እና በቂ የአየር ዝዉውር እንዲኖር የማድረግ ግዴታ የሚቀጥል ይሆናል።

_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here