የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ”ከኢድ እስከ ኢድ ወደ አገር ቤት” ተጓዦች የ20 በመቶ ቅናሽ አደረገ

0
885

ሐሙስ መጋቢት 29 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የታላቁ ጉዞ ወደ አገር ቤት ጥሪ ኹለተኛ ክፍል የሆነው “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ አገር ቤት” ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአየር ጉዞ ትኬት ዋጋ ላይ የ20 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።

በዚሁ መሰረት ወደ አገር ቤት ተጓዦች ትኬታቸውን ከፈረንጆቹ ሚያዝያ 6 እስከ ሚያዝያ 21 ቀን 2022 በመቁረጥ እና ጉዟቸውን ከሚያዝያ 25 እስከ ግንቦት 15 ቀን 2022 ድረስ በማመቻቸት የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አየር መንገዱ ጋብዟል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲም ተጓዦቹ ወደ አገር ቤት ከመጡ በኋላም በተዘጋጁላቸው ልዩ ልዩ መርሀ ግብሮች ላይ እንዲታደሙም ጥሪውን አቅርቧል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here