10 የኬሚካል ማዳበሪያ ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡ አገራት

0
1161

ምንጭ፡- ስታቲስታ (2020)

ዓለም ሥልጣኔን ተዋወቅሁ ባለች ማግስት ከተፈጥሮ ‹የሚስተካከሉ› ሰው ሠራሽ ግኝቶችን ጥቅም ላይ ለማዋል ደፋ ቀና ሲባል ነበር። የተሳካ ይመስላል፤ ግን ያስከፈለውና የሚያስከፍለው ዋጋ ቀላል አይደለም። የተፈጥሮን ማዳበሪያ ጣጥለው የኬሚካሉ ላይ ጥገኛ የሆኑ የእርሻ መሬቶችና አርሰው አደሮችም አሁን ላይ ከተፈጥሮ መራቅና ሰው ሠራሽ ኬሚካል ላይ ጥገኛ የመሆን ችግሩ ግልጥ እየሆነላቸው ይመስላል። በአንጻሩ የኬሚካል ማዳበሪያ አቅራቢዎች ገቢያቸውን ለመጨመር አልፎም ጥገኞችን ለመፍጠር እድል ፈጥሮላቸዋል።
ስታቲስታ የተባለውና የቁጥር መረጃዎችን ይፋ የሚያደርገው ድረገጽ፣ ልክ እስካለፈው ዓመት አድሶ ባቀረበው መረጃ መሠረት፣ በዓለማችን ቁጥር አንድ የኬሚካል ማዳበሪያ ለውጭ ገበያ አቅራቢ አገር ሩስያ ናት። ከዐስርቱ ከፍተኛ የኬሚካል ማዳበሪያ ላኪዎች መካከል አፍሪካዊቷ ሞሮኮ 3.4 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያለውን ማዳበሪያ በመላክ በአምስተኛ ደረጃ ላይ ተገኝታለች።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here