የኢትዮጵያ የቱሪስት መረጃ ስርዓት ውስንነት ነበረበት

0
713

ከአሁን ቀደም በኢትዮጵያ የነበረው የቱሪስት ስታትስቲክስ ስርዓት ውስንነት እንደነበረው የኢፌዲሪ ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህንም መሰረት በማድረግ ስርዓቱን በማዘመንና ጠቃሚ ማሻሻያዎችን በማድረግ ትክክለኛ መረጃዎችን ለማሰባሰብና ለማደራጀት የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ከዚህም በመነሳት ወደ አገር ውስጥ የገቡ ጎብኚዎችን ቁጥር፣ የተገኘ ገቢ መጠንና ጎብኚዎች ግለ ታሪክ ከቀድሞ በተሻለ መልኩ ማደራጀት ተችሏል።

እንደ ሚኒስቴሩ ገለፃ በ2011 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ውስጥ 505 ሺሕ 769 የውጭ ጎብኚዎች ወደ አገር ውስጥ የገቡ ሲሆን 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ለመረዳት ተችሏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 24 ሚያዚያ 12 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here