ኢትዮጵያን ከኤርትራ በሚያዋስነው ድንበር ላይ ያለው የሑመራ በር – እምኒሓጀር ሐሙስ፣ ሚያዝያ 10 ጠዋት እንደተዘጋ የሁመራ ነዋሪዎች ለቢቢሲ አማርኛ ገለፁ።
የሁመራ ከተማ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ይብራህ የማነ መንገዱ ባሳለፍነው ሐሙስ ጠዋት አንድ ሰዓት ላይ እንደተዘጋ ተናግረዋል።
በጥበቃ ላይ የሚገኙት የኤርትራ ወታደሮች፣ መኪኖች እንዳይገቡና እንዳይወጡ እንዲከለክሉ እንደታዘዙና የቆየው የንግድ ልውውጥ እንደቆመ ይብራህ ተናግረዋል።
መኪኖች በኹለቱም ወገኖች መግባትና መውጣት እንዳልቻሉ የተገለጸ ሲሆን፣ በእግራቸው የሚመላለሱ ሰዎችም እንዳይገቡና እንዳይወጡ ተደርጓል።
ቅጽ 1 ቁጥር 24 ሚያዚያ 12 ቀን 2011



