መንግሥት በሦስት ወራት 22 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የበጀት ጉድለት ገጠመው

0
500

በ2011 ኹለተኛ ሩብ ዓመት 22 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት መንግሥት ገጥሞት እንደነበር በባለፈው ሳምንት የወጣው የብሔራዊ ባንክ ሪፖርት አመላከተ።

ባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የስድስት ቢሊዮን ብር ጭማሪ ጉድለት ማሳየቱ ታውቋል።
በኹለተኛ ሩብ መንግሥት ያወጣው ወጪ 80 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ሆኖ ሲመዘገብ 57 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ገቢ ከታክስና ሎሎች ምንጮች ተሰብስቧል። በተመሳሳይ ወቅት 3 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ብድር ለመክፈል መንግሥት ማውጣቱ ታውቋል።

በቅርቡ የገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ 33.9 ቢሊዮን ብር ፓርላማ ማፅደቁ ይታወሳል። ይህም የ2011 በጀት ዓመት ጉድለትን ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ቅጽ 1 ቁጥር 24 ሚያዚያ 12 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here