የ22 ዓመቷ ሱዳናዊት አብዮተኛ የፖለቲካ ፍላጎት የለኝም አለች

0
455

ሱዳንን ለ30 ዓመታት ሲያስተዳድሩ የነበሩትን ዖማር አል-በሽርን ከሥልጣን በማውረድ ወደ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግበት ዘብጥያ ያወረደው የአደባባይ ተቃውሞ ከተጀመረበት ዕለት ጀምሮ ስትሳተፍ እንደቆየች የምትናገረው አላ ሳላህ የአብዮቱ ምልክት ተደርጋ በዓለም ዙሪያ ስትወደስ ከርማለች።

ʻታውራʼ በሚለው ዜማዊ ተቃውሞዋ የእስልምና ሃይማኖትን ለአምባገነን ስርዓታቸው ሽፋን አድርገው ቢጠቀሙበትም ሃይማኖቱ ጥፋት እንደሌለው መልዕክት የሚያስተላልፉት ግጥሞቿ የሱዳን ወጣቶችን ልብ ከማነሳሳት አልፎ በዓለም ዙሪያ ሚሊዮኖች ተመልክተውታል።

ለዘጋርዲያን በሰጠችው ቃለ ምልልስም ምንም ዓይነት የፖለቲካ ዓላማ እንደሌላት፤ እንዲሁም አገሯ ሱዳን ከየትኛውም የፖለቲክ አስተሳሰብ በላይ መሆኗን ጭምር ተናግራለች።

ፈጣን የሆኑ ለውጦችን እያስተናገደ የሚገኘው የሱዳን አብዮት ከአፍሪካ ኅብረት እንዲሁም፣ አሁንም ከአደባባይ ባልተመለሱት ወጣቶች ጥያቄ መናጡን ቀጥሏል። የአፍሪካ ኅብረት ባሳለፍነው ሳምንት ለወታደራዊው መንግሥት በ15 ቀን ውስጥ ሥልጣን ለሲቪል እንዲያስረክብ ቀነ ገደብ መስጠቱ እንዲሁም፣ የወታደራዊው መንግሥት በመጀመሪያው ጉብኝቱ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር መነጋገራቸውም አይዘነጋም።

ቅጽ 1 ቁጥር 24 ሚያዚያ 12 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here