‘ሰብ ሕድሪ ሲቭል ማሕበረሰብ ትግራይ’ አመራሮቼ እስርና ማዋከብ እየደረሰባቸው ነው አለ

0
578

ሰብ ሕድሪ ሲቭል ማሕበረሰብ ትግራይ የተሰኘው የሲቪክ ተቋም አመራሮቹና አባላቱ በትግራይ ክልል እስርና ማዋከብ እየገጠማቸው መሆኑን አስታወቀ። ማኅበሩ ዴሞክራሲ የሰፈነበት ሥርዓት እንዲታነፅ፤ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ፤ ከሙስና የፀዳ ስርዓት እንዲኖር ለመሥራት የተቋቋመ መሆኑን ያስታወቁት ሊቀ መንበሩ መሐሪ ዮሐንስ፣ ማኅበሩ ችግር የገጠመው ከምሥረታው ጀምሮ መሆኑን ማክሰኞ፣ ግንቦት 13 በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

ከትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ ሕጋዊ ፍቃድ አግኝቶ በክልሉ መንቀሳቀስ የጀመረው በሰኔ 2010 ሲሆን በተለያዩ የትግራይ ከተሞች እየተንቀሳቀሰ በትግራይ ሕዝብ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እንዲሁም ምጣኔ ሀብታዊ ችግሮች ዙርያ ከሕዝብ ጋር በሚያደርገው ውይይት ዕንቅፋቶች እየገጠሙት እንደሆነ በመግለጫው አስታውቋል።

የሰብ ሕድሪ ሲቪክ ማኅበረሰብ ትግራይ ሊቀ መንበር መሐሪ ዮሐንስ “ከምሥረታ ጀምሮ ይገጥመን የነበረ ችግር አሁን ተባብሶ አባላቶች እና ደጋፊ እስከማሰር እንዲሁም ማንገላታት ደርሷል” ይላሉ።

በቅርቡ የሲቪክ ተቋሙ ሊቀ መንበርን ጨምሮ ሰባት አባላት በትግራይ ክልል ፅጌረዳ ከተማ ከሕዝብ ጋር በአስተዳደር ችግሮች ዙርያ ለመወያየት በተጓዙበት ታስረው ከፍተኛ እንግልት ደርሶባቸው መለቀቃቸውን ተቋሙ በምሳሌነት ጠቅሷል። በትግራይ ክልል ክልተ አውላዕሎ ወረዳ ሰብ ሕድሪ በጠራው ስብሰባ ተገኝታችኋል የተባሉ የሕዝባዊ ውይይት መድረክ ተሳታፊዎችም ታስረዋል፣ ተንገላተዋል፣ ማስፈራርያም ደርሶባቸዋል ብለዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 29 ግንቦት 17 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here