የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሦስት ቋንቋዎች የጥሪ ማዕከል ሊጀምር ነው

0
509

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሶማልኛ፣ ትግርኛና ኦሮምኛ ቋንቋዎች የመረጃ ማዕከሉን በማደራጀት የስልክ ጥሪ አገልግሎት ለመጀመር ለኢትዮ ቴሌኮም 3 ሚሊዮን ብር ክፍያ መፈጸሙን ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ።

ባንኩ በአሁን ሰዓት በኹለት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች አገልግሎት እየሠጠ ሲሆን አዲስ ለሚጀምራቸው ሦስት አዳዲስ ቋንቋዎችም ከአራት እስከ አምስት ዓመት የሥራ ልምድ ያላቸውና በቋንቋ ክህሎት ያላቸው የተቋሙ ሠራተኞችን ቅጥር መጀመሩም ታውቋል።

የጥሪ ማዕከሉ የሚሰጠው ግልጋሎት ሙያዊ ክህሎት የሚያስፈልገው ነው በመባሉ ከተለያዩ ቅርንጫፎቹ የባንኩን ሠራተኞች በውስጥ ማስታወቂያ አውጥቶ ለመቅጠር ዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ከንግድ ባንክ ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት ወደ ሥራ ለመግባት የቻይና ኩባንያ የሆነው ሁዋዊ ጋር በመነጋገር ላይ መሆኑም ታወቋል። በ951 ነጻ የጥሪ ማዕከል የሚስተናገዱት በባንኩ የሚሠጡ አገልግሎቶች፣ በባንኩ ዕለታዊ ምንዛሬ ተመን አገልግሎቶችን በእንግሊዝኛ እና በአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ቅጽ 1 ቁጥር 29 ግንቦት 17 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here