የኢትየጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) በአምስት መስመሮች ሕዝብን ለማደራጀት ያሰማራቸው አመራሮቹና አባላቶቹ በአንዳንድ የዞንና ወረዳ አመራሮች ጭምር እንቅስቃሴውን ለመግታት ተሞክሮ እንደነበር አስታወቀ። በኦሮሚያ እና በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች ክልሎች ችግሮች እንዳጋጠማቸው ገልጸዋል። በሕዝቡ ውስጥ ተንቀሳቅሰው ማንኛውን ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ እንዲሁም የአባላት ምልመላ እንዳያካሒዱ ተደርጓል።
እነዚህ እንቅስቃሴዎች የቅስቀሳ ሥራውን እንዳስተጓጎሉበትም ፓርቲው ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።
ቅጽ 1 ቁጥር 31 ሰኔ 1 ቀን 2011



