በቀን 80 ሺሕ ዳቦ የሚያመርት ፋብሪካ ሊገነባ ነው

0
1095

በአዲስ አበባ ከተማ በስድስት ወራት ውስጥ ግንባታው የሚጠናቀቅ አዲስ የዳቦ ፋብሪካ ግንባታ ባለፈው ሐሙስ፣ ግንቦት 29 የመሰረት ድንጋይ በከተማው ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና የሚድሮክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚው በአብነት ገብረመስቀል ተቀመጠ። በስምንት መቶ ሚሊዮን ብር በሆራይዘን ፕላንቴሽን የሚገነባው ፋብሪካ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ውስጥ እንደሚሆን ታውቋል።
በመንግሥት የሚደጎሙ ዳቦ ቤቶች በ1 ብር ከ30 ሳንቲም የሚሸጡትን መቶ ግራም ዳቦ በ0.75 ሳንቲም ለማቅረብ ያቀደው ፋብሪካው በቀን 80 ሺሕ ዳቦ ይጋግራል ተብሎ ይጠበቃል። ከመንግሥት ድጎማ ውጪ ያሉ ዳቦ ቤቶች በአማካኝ አንድ ዳቦ በ 2 ብር ከሃምሳ የሚሸጥ ሲሆን አዲሱ ፋብሪካ ሲጀምር የዳቦ ዋጋን ያረጋጋል ተብሎ ይጠበቃል። ከንቲባውም መንግሥት ከግል ባለሀብቱ ጋር በመሆን ለኅብረተሰቡ መሰረታዊ የሆኑ አቅርቦቶችን በዝቅተኝ ዋጋ ያቀርባል ሲሉ ተናግረዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 31 ሰኔ 1 ቀን 2011

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here