የአፍሪካ ኅብረት ሱዳንን ከአባልነት ከሐሙስ፣ ግንቦት 29 ጀምሮ አገደ። በዋና ከተማዋ ካርቱም ወታደራዊው መንግሥት በተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ በወሰደው እርምጃ የብዙ ሰዎችን መገደል ተከትሎ ነው ኅበረቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው።
ተቃውሞውን የሚያስተባብሩት የተቃዋሚ የመብት ተሟጋቾች እንደሚገልፁት በሰላማዊ ሰልፈኞቹ ላይ በተወሰደ እርምጃ 108 መገደላቸውን አስታውቋል፤ ወታደራዊው መንግሥት ግን ሟቾቹ 46 ብቻ መሆናቸውን አምኗል።
ተቃውሞው የተባባሰው ከሰኞ፣ ግንቦት 26/2011 ጀምሮ በመዲናይቱ በሚገኘው የወታደራዊው ዋና መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ተቀምጦ ተቃውሞን የመግለጽ እንቅስቃሴን ተከትሎ መሆኑ ታውቋል። በተቃዋሚዎች ኀይሎች እና በወታደራዊው መንግስት መካከል ሲካሔድ የነበረው ንግግር ያለፈው ሐሙስ መቋረጡን ተከትሎ, የእንግሊዝ መንግሥት በአገሩ የሚገኙትን የሱዳን አንባሰደር ውጪ ጉዳይ መሥራቤቴ ድረስ እንዲመጡ በማስጠራት ያለውን ሥጋት ገልጿል።
የቀድሞው ፕሬዘዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር በሰላማዊ ተቃውሞ ከሥልጣን ከተወገዱ ካለፈው ሚያዚያ ወዲህ በዚህ ሳምንት ወታደራዊው መንግሥት የወሰደው እርምጃ ብዙ የሞት አደጋ ደርሷል።
ቅጽ 1 ቁጥር 31 ሰኔ 1 ቀን 2011



