ንግድ ባንክ የትራፊክ ቅጣት መሰብሰብ ሊጀመር ነው

0
563

የአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ከሰኔ 5/2011 ጀምሮ የትራፊክ ቅጣት ክፍያ ስርዓትን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ተፈጻሚ ለማድረግ ውሳኔ ላይ መድረሱን አስታወቀ። ከዚህ ቀደም በዘጠኙ የኤጀንሲው የክፍያ ማዕከላት በተጨማሪ በ ‹ለሁሉ› የቅጣት መሰብሰቢያ ማዕከላት ሲሰበሰብ የነበረው የቅጣት ገንዘብ በድንገት በመቆሙ በጥቂት ደቂቃዎች የሚያልቅ ክፍያ ሰዓታትን መውሰድ መጀመሩ ታውቋል።

አዲስ ማለዳ ቅኝት ባደረገችበት በልደታ ቅርንጫፍ ከተሰለፉ 200 ከሚጠጉ ተገልጋዮች መካከል አንዱ የሆነው ሰዒድ የግንባታ ዕቃዎች በመጫን የሚተዳደር ሲሆን ቅጣት እንዲከፍል ከተወሰነበት ዐሥራ አምስት ቀናት ቢያስቆጥርም እስካሁን መክፈል አለመቻሉን ይናገራል። ሥራው ከከተማ ውጭ በመሆኑና ለቅጣት ክፍያ ማራዘሚያ ቢፃፍለትም በትራፊክ ፖሊሶች አልከፈልክም ጥያቄ ሥራውን በአግባቡ ለመሥራት አለመቻሉን ተናግሯል። በተለይም ለሕዝብ ማመላለሻ ተሽካርካሪዎች ቅድሚያ ያለመሰጠቱ ድርብ ጉዳት እያስከተለ መመልከቱን ተናግሯል።

‹ለሁሉ› ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ጋር ባሰረው ውል መሠረት ለዓመታት አገልግሎት እየሠጠ የቆየ ሲሆን በተያዘው የበጀት ዓመት ውሉ እንደሚጠናቀቅ ነገር ግን ውሉ ከመጠናቀቁ በፊት የቴሌ ፋይበር ኦፕቲክስ በመቋረጡ ሥራው መስተጓጎሉ ታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 31 ሰኔ 1 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here