10ቱ በአፍሪካ ብዙ የሞባይል ተጠቃሚ ያሉባቸው አገራት

0
733

ምንጭ፡-አፍሪካ ዲጂታል አውትሉክ 2019 (እ.ኤ.አ)

የአፍሪካ የቴሌኮም ኢንዱስትሪ ላለፉት 20 ዓመታት በየዓመቱ በአማካኝ 30 በመቶ ዕድገት በማሳየት ከኤሲያ ቀጥሎ በዓለም ኹለተኛ ትልቁ የገበያ ባለድሻ ሆኗል። በ2018 (እ.ኤ.አ) በአፍሪካ የሞባይል ተጠቃሚዎች ቁጥር ከቀደመው ዓመት ከነበረበት አንድ ቢሊዮን ወደ 1 ነጥብ 04 ቢሊዮን በመጨመር የአሕጉሪቱን የሞባይል ተጠቃሚነት ቁጥር 82 በመቶ አድርሶታል።

በሕዝብ ብዛት በአፍሪካ አንደኛ የሆነችው ናይጄሪያ በአፍሪካ ብዙ የሞባይል ተጠቃሚ ያላት አገር ስትሆን ኢትዮጵያም ባለፉት 20 ዓመታት ዕድገት በማሳየት ቀላል በማይባል የኢንዱስትሪ መስፋፋት አሳይታለች። የኢትዮጵያ የቴሌኮም ሴክተር ላይ መንግሥት በቅርቡ ሊያደርግ ባሰበው ማሻሻያ ገበያውን ከመንግሥት ብቸኛ የገበያ ቁጥጥር ነፃ በማውጣት ለግል ባለሀብቶች በሩን ይከፍታል ተብሎ ይጠበቃል።

ለዚህም ዓለማቀፍ ድርጅት በመቅጠር ሀብቱን በማስገመት ላይ ያለው ቴሌኮሙ በዚህ ሳምንት እንዲቋቋም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፀደቀው አዋጅ ይህንን ለውጥ የሚመራውን ኤጀንሲ በማቋቋም ሒደቱን እንደሚጀምር ይጠበቃል።

ቅጽ 1 ቁጥር 32 ሰኔ 8 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here